የሳይንስና ቴክኖሎጂ ጥናት ምርምር ፣አቅም ግንባታ ዳይሬክቶሬት

የዳይሬክቶሬቱ መግለጫ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሳይንስና ቴክኖሎጅ ጥናት ምርምር እና አቅም ግንባታ ዳይሬክቶሬት የሳይንስና ቴክኖሎጂ ጥናት፣ ምርምርና ፈጠራ ፣ የሰው እና የተቋማት አቅም ግንባታ፣የሳይንስና ቴክኖሎጂ ቢዝነስና ኢንተርፕሪነርሺ እንዲሁም የኢኖቨሽንና የኢሜርጅንግ ቴክኖሎጂ ሽግግር ስራዎችን ተግባራዊ ያደርጋል፡፡ በተጨማሪም ዳይሬክቶሬቱ የሳይንስና ቴክኖሎጅ የምርምር ፕሮቶኮል፣ ስነ-ምግባርና ፖሊስ ክትትል በማደረግ ጥራት ያለው የምርምር ዉጤቶችን የመደገፍና የማበረታታት፤ የማስረፅ፤ በሳይንስና ቴክኖሎጅ ምርምር ላይ የማማከር፣ የመደገፍ እንዲሁም የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ከህበረተሰቡ እና ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር እንዲስፋፋ የማድረግና በተመረጡት ቦታዎች የልቀት ማዕከላት የመቋቋም ዓላማ አለው፡፡ በተጨማርም የሳይንስና የቴክኖሎጅ የረጅምና የአጭር ጊዜ ስልጠናዎች በማዘጋጀትና መስጠት፤ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር ትስስር በመፍጠር የቴክኖሎጂ ስልጠና ዕድሎችን በመፍጠር ተጠቃሚ በማድረግ፣ የእውቀት ሽግግር የሚደረግባቸው ሴሚናሮች እና ወርክሾፖችን ማዘጋጀት እና በማሳተፍ ፈፃሚዎች የላቀ የሳይንስና ቴክኖሎጂ አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያደርጋል፡፡ ዳይሬክቶሬቱ የግለሰብ የእውቀት እና የተቋም ኦርጋናይዜሽናል ሚሞሪ  (Knowledge Management and organizational Memory) የማደራጀት ላይ በመስራት የተማከለ የተቋም እና የግለሰብ የመረጃ/ዕወቀት ፍላጎት ተደራሽና ተጠቃሚ የማድረግ ዓላማ ይዞ የተቋቋመ ነው፡፡

የዳይሬክቶሬቱ ዋና ዋና ተግባራት

 • የሳይንስና ቴክኖሎጂ ጥናትና ምርምር
 • የሳይንስና ቴክኖሎጂ የምርምርስነ-ምግባር መሰረት መከናወኑን ማረጋገጥ
 • ሊቪንግላብ (Living Lab) ማመቻቸት
 • በሳይንስናቴክኖሎጂምርምር ላይ ማማከር
 • የሳይንስና ቴክኖሎጂ ምርምር ስርጸት
 • የልህቀት ማዕከል ማደራጀት
 • የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሽግግር
 • የአርትፍሻል ኢንቲሌጀት ቴክኖሎጂ ሽግግር
 • የማቴርያል ሳይንስን ቴክኖሎጅ ሽግግር
 • የባዮ ቴክኖሎጅ ጥናትና ሽግግር ቴክኖሎጂ ምርምር
 • የምልስ ምህንድስና ቴክሎጂ ማስፋፋት
 • በተመረጡ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፎች ላይ የስራ ዕድል ፈጠራ
 •  ምርጥ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ቢዝነስ ኃሳብ ያላቸውን ወደ ስራ ማስገባት
 • የቢዝነስእናቴክኖሎጂልማትአገልግሎት
 • ፋይናንስና የሎጂስቲክድጋፍማድረግ/ማመቻቸት
 • የገበያ/ኢንዱስትሪትስስር
 • የሳይንስና ቴክኖሎጂ ስልጠና
 • የሳይንስና ቴክኖሎጂ ቤተ ሙከራእና የመስክ ፍተሻ ስራዎች
 • ሴሚናሮች እና ወርክሾፖች ዝግጅት
 • ለተመረጡ የፈጠራ ስራዎች የማበረታቻ ሽልማቶችን መስጠት
 • የቴክኖሎጂ ዞን መለየትና ወደሰራ ማስገባት
 • የሳይንስ ካፌዎችን ማደራጀት
 • ተቋማዊ ዕውቀት መገንባት (Organization Memory)
 • ዕውቀት ማኔጅምንት (Knowledge Management)
 • የዩኒቨርሲቲዎችና/ኢንዱስትሪ ትስስር