ወቅታዊ ጉዳዮች ወቅታዊ ጉዳዮች

Back

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ ከዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመተባበር የሚያስጠናቸዉን ፕሮጀክቶች ዛሬ በይፋ አስጀመረ፡፡

 

ኤጀንሲያችን የመንግስት ክላውድ መረጃ ማዕከል ኮምፕዩቲንግ፤ የመንግስት አውታረ መረብ እቅድ፤ስማርት ሲቲ ፕላን፤ የኤሌክትሮኒክ ዌስቲንግ አስተዳደር ስርዓት፤ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለመተግበር እንዲያስችል ሳይንሳዊ ጥናት ለማድረግ ተወዳድሮ  ላሸነፋት ዩኒቨርሲቲዎች ስራዉን በይፋ አስጀምሯል፡፡

በእለቱ በክብር እንግድነት የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪሲና ሰዉ ሃብት እስተዳደር የሆኑት አቶ ሃይሉ ሉሌ እንደተናገሩት  የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር ከተማዋን በአገልግሎት አሰጣጥ፤ ዘመናዊ የአኗኗር ዘይቤ ለመፍጠር   እና ዉብና ጽዱ ለማድረግ የሳይነስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ማሳደግና  መጠቀም   የግዴታ በሆነበት በዚህ ዘመን ላይ እነዚህን ለሁለንተናዊ እድገት ወሳኝ የሆኑትን ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ  የአዲስ አበባ  ሰይንስና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ እያደረገ ያለዉ ጥረት የሚደነቅ መሆኑን ገልጸዉ በጋራና በመተባበር ከሰራን የምንፈልገዉን ዉጤት ማምጣት እንደሚቻል ገልጸዋል፡፡ 

የኤጄንሲዉ ዋና ዳይሬክተር አቶ አብርሃም ሰርሞሎ በበኩላቸዉ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ላይ ጥናትና ምርምር ከሚያደርጉት  ተቋማት ጋር አብሮ በመስራት  በምርምር የተገኘዉን እዉቀት ወደ ተግባር በመቀየር አንደ ሌሎች ያደጉት አለም ከተሞች ሁሉ  ከተማችንን ስማርት ሲቲ ለማድረግ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰሩ ተናግሯል፡፡

ጥናቱን ለማድረግ የተረከቡት ዬኒቨርሲቲ ተወካዮችም የደጉት አገሮች ላይ ከፍትኛ የትምህርት ተቋም በጥናትና ምርምር አገራቸዉን አንዳበለጸጉት ሁሉ የአዲስ አበባ ሳይንስና ገቴክኖሎጂ ኤጀንሲም በጋራ ለመስራት ቁርጠኛ መሆኑ ከማስደሰቱም በላይ በዘርፋ ያላቸዉን እዉቀትና ልምድ በማጋራት የተጀመረዉን ዲጂታል ትራንስፎርሜሸን ስኬት ለማፋጠን  ጥናቱን በተገቢዉ ሁኔታ በማጥናት ግኝቱን በተቀመጠላቸዉ ጊዜ ይፋ እንደሚያደርጉ  ተናግሯል፡፡


የዋና ዳይሬክተሩ መልዕክት

አዲስ አበባ ከተማ የኢትዮጲያና የአፍሪካ መዲና የሆነች በዓለምም በቀዳሚነት ከሚጠቀሱ ታሪካዊና ዲፕሎማሲያዊ ከተሞች አንዷ ነች፡፡ ከተማችን ሁሉንም ዓይነት ማህበረሰብ ያቀፈች፣ ለሃገራችን ስልጣኔም ፈር ቀዳጅ ሚናን የምታበረክት፣ በአጠቃላይ በኢኮኖሚ፣ በፖለቲካ እና በማህበራዊ መስኮች ለማሳከት ለምናስበው የብልጽግና ጉዞ የላቀ ድርሻ ያላት መሆኗ ለሁሉም ግልጽ ነው፡፡ Read More About የዋና ዳይሬክተሩ መልዕክት »

ማህበራዊ ድረ-ገፅ ማህበራዊ ድረ-ገፅ

Back

ስኮር ካርድ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሳይንስና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ የ2013-2022 .ም ስትራቴጂ እቅድ

የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ ስትራቴጂያዊ ስኮር ካርድ BSC Scorecard CORPORATE-FinalDraft 2013 e.c

 የዳታ ማዕከልና ክላውድ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት BSC Scorecard DIRECTORATES-Cloud 2013 e.c

የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት ግንባታ ዳይሬክቶሬት BSC Scorecard Infrastructure 2013 e.c

የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ኦፕሬሽን ማዕከል BSC Scorecard IT Operation 2013 e.c

የሳይንስና ቴክኖሎጂ ጥናት፤ ምርምር እና አቅም ግንባታ ዳይሬክቶሬት BSC Scorecard Resarch 2013 e.c

የመረጃ ደህንነት ዳይሬክቶሬት BSC Scorecard Security 2013 e.c

የሶፍትዌር ሲስተም ልማት ዳይሬክቶሬት BSC Scorecard Software 2013 e.c

የስትራቴጂና ጥራት መሰረተ ልማት ዳይሬክቶሬት BSC Scorecard Strategy 2013 e.c

ሴክተር BSC Scorecard SECTORS-All-Updated 2013 e.c

ክፍለ ከተማ BSC Scorecard SUBCITY-All-Updated 2013 e.c

 ከተማ ጨረታ