የኤጀንሲያችን ስልጣን፣ ተግባርና ኃላፊነት

 1. የልማት ፍላጐት መሰረት ያደረገ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ ምርምርና ልማት እቅዶች ያዘጋጃል፤ ሲፀድቅም ተግባራዊ ያደርጋል፤
 2. የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን እንቅስቃሴዎችን በበላይነት ያስተባብራል፤ በኢንዱስትሪዎች፣ ዩኒቨርስቲዎች፣ የምርምር ተቋማት እና ቴክኒክና ሙያ ተቋማት መካከል ጠንካራ ትስስርና ትብብር እንዲፈጠር ያደርጋል፤
 3. የኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ ልማትን አስመልክቶ ተገቢውን መረጃ መከታተል፣ ማሰባሰብና መተንተን የሚያስችል ሥርአትና ከተማ አቀፍ አቅምን ይገነባል፤
 4. የአስፈፃሚ ተቋማት አገልግሎት አሰጣጣቸው በኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ የተደገፈ እንዲሆን ያደርጋል፤ ደረጃ በደረጃም ለተጠቃሚዎች በቀጥታ አገልግሎት ሊሰጥ በሚችሉበት ሁኔታ መመቻቸታቸውን ያረጋግጣል፤
 5. የኢንፎርሜሽን ከሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት ክፍተትን ይለያል፤ አስፈላጊ መስፈርቶችን በማዘጋጀት ለሚመለከተው አካል ያቀርባል፤ ሲፈቀድም ይዘረጋል፤ እንዲዘረጋም ያደርጋል፤
 6. ደረጃ አውጥቶ ወይም በወጣው ደረጃ መሰረት ሃርድዌርና ሶፍትዌር ያዘጋጃል፤ እንዲዘጋጅ ያደርጋል፤ ለአስተዳደሩ መስሪያ ቤቶች ያቀርባል፣ ተግባራዊ መሆኑን ይከታተላል፤ በዚህ መልኩ ለሚያዘጋጃቸው የኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ ስም ይሰጣል አጠቃቀም ጋር በተያያዘ የአስተዳደሩን መስሪያ ቤቶች ያማክራል፤
 7. የከተማ አስተዳደሩ ተቋማት የኮምፒውተር መረቦችና አፕሊኬሽኖች እንዲቀናጁና እንዲናበቡ ያደርጋል፤ ያረጋግጣል፤
 8. የከተማ አስተዳደሩን የመረጃ ስርዓት ያደራጃል፤ ጥራቱ፣ ደህንነቱና አስተማማኝነቱን ይጠብቃል፤
 9. በከተማው ውስጥ የኮፒውተር መረብ ዝርጋታ ስራዎችን ለሚሰሩ አካላት በጥናት ላይ የተመሰረተ ፈቃድ ይሰጣል፤
 10. ከሚመለከታቸው ሌሎች አካላት ጋር በመተባበር በከተማ አስተዳደሩ የቴክኖሎጂ ፖርኮች እንዲቋቋሙ ያደርጋል፤
 11. የሳይንስና ቴክኖሎጂ እንቅስቃሴዎች የገንዘብና የዓይነት የማቴሪያልና የቴክኒክ ድጋፎች የሚያገኙበትን ስርዓት ይዘረጋል፤
 12. የአዕምሯዊ ንብረት መብት ጥሰቶችን ለመከላከልና የህብረተሰቡ ግንዛቤ ለማሳደግ ከሚመለከታቸው የፌደራል አካላት ጋር በመተባበር ይሰራል፤
 13. የጥራት መሰረተ ልማትና የጨረራ እና ጨረራ አመንጪ መከላከያ እንቅስቃሴዎችን ያስተባብራል፤ ለተግባራዊነቱም የበኩሉን ጥረት ያደርጋል፤
 14. የምርምር ኘሮቶኮሎች ሥነ-ምግባርን ተከትለው መካሄዳቸውን ይከታተላል፤ የሥነ-ምግባር ጉድለት ሲያጋጥም አስፈላጊ የሆኑ ሕጋዊ እርምጃዎች እንዲወሰዱ ጥረት ያደርጋል፤
 15. የምርምር ሥራዎች /ኘሮቶኮሎች/ እና የባዮኢቲክስ ምርምሮች ውጤታማ በሆነ መልኩ እንዲተገበሩ ለማድረግ እንዲቻል ሥራውን በበላይነት የሚመራ አካል እንዲቋቋም ሀሳብ ያቀርባል፡፡