የሳይንስና ቴክኖሎጂ ስትራቴጂና ጥራት መሰረተ ልማት ዳይሬክቶሬት

vየዳይሬክቶሬቱ  መግለጫ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ ስትራቴጂና ጥራት መሰረተ ልማት የሚያከናዉናቸዉ ዋና ዋና ተግባራት ዉስጥ የስትራቴጂና ስታንደርድ ማዘጋጀት ፣ የጥራት መሰረተ ልማትና የጨረራ ቁጥጥር ፣ የቴክኖሎጂ ኦዲትና የአዕምሮአዊ ንብረት ጥበቃ እና የስራ ፊቃድ ሲሆኑ በአጠቃላይ በከተማ አስተዳደሩ ሳይንስና ቴክኖሎጂ የሚመራበትን የተለያዩ ስታንደርዶችን፣ ፖሊሲዎችና መመሪያዎችን በማዘጋጀት የቴክኖሎጂ ህጋዊ ስርዓትና ደህንነት ማረጋገጥ አላማ አለው፡፡  የዚህ ሕግ የማስፈጸም ዝርዘር የሥራ ቅደም ተከተል (procedure) ዋና ዓላማ የጥራት መሰረተ ልማቶችን፣ ጨረራ አመንጪዎችና ተግባራት የሪጉላቶሪ ቁጥጥር ቡድን መሪ ውስጥ ሕግ በማስፈጸም (Enforcement) ሂደት ወቅት ሊወሰዱ የሚገባ የስራ ቅደም ተከተል በማውጣት በሁሉም የሚመለከታቸው አካላት ዘንድ ግልፅና ወጥ የሆነ ሕግ የማስፈፀም እና የክትትል  ስርዓት እንዲኖር፣  የስራ ቅደም ተከተል ጠብቀው ሥራዎች በአግባቡ እንዲከናወኑ ለማስቻል ነው፡፡ በሌላ በኩል ዳይሮክተሬቱ የቴክኖሎጂ ኦዲት በማድረግ በቴክኖሎጂ መሰረተ ልማትም መሰረት ያደረገ የመረጃ ልውውጦች ላይ ምርመራ ያደርጋል፡፡ በተጨማሪ ዳይሮክተሬቱ የአዕምሮአዊ ንብረት ጥበቃ ከሚመለከታቸዉ ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር የባለቤትነት ማረጋገጫ እንዲሰጣቸዉ በማድረግ በዘርፉ በከተማዉ የኮምፒዉተር መረብ ዝርጋታ ስራዎች ለሚሰሩ የስራ ፊቃድ ይሰጣቸዋል፡፡

vየዳይሬክቶሬቱ ዋና ዋና ተግባራት

 • መመሪያ ማዘጋጀት
 • ስትራቴጂና ፊውቸር ፕላኒግ
 • ስታንዳርድ ማዘጋጀት
 • አክርዲቴሽን
 • የተስማሚነት ምዘና
 • የጨረራ አመንጪ ቴክኖሎጂዎች ቁጥጥር
 • የንጹህ ቴክኖሎጂና ስነ-ህይወት ጥበቃ
 • የቴክኖሎጂ ኦዲት
 • የመሰረተ ልማት ጥራት ማረጋገጥ
 • የመረጃ ደህንነትና የግላዊ ጥበቃ
 • የአዕምሮአዊ ንብረት ጥበቃ
 • በኮምፒዉተር መረብ ለተሰማሩ የስራ ፍቃድ መስጠት